# ሸክም ሸክም ከባድ ጫና ነው። ቃል በቃል የጥንት እንስሳት የሚሸከሙትን ሸክም ያመልክታል። “ሸክም” የሚለው ቃል በርካታ ምሳሌያዊ ትርጕሞችም አሉት። * ሸምክ አንድ ሰው መፈጸም ያለበትን ከባድ ሥራን ወይም ጠቃሚ ኀላፊነትንም ማመልከት ይችላል። ከባድ ሸክም፣ “ተሸክሞአል” ወይም፣ “ከባድ ጫና ተጭኖታል” ማለት ይቻላል። * አንድ ጨካኝ መሪ ሕዝቡ ላይ ከባድ ሸክም ሊጭን ይችላል፤ ለምሳሌ ብዙ ግብር ወይም ቀረጥ እንዲከፍሉ በማስገደድ። * ሌላው ላይ ሸክም መሆን የማይፈልግ ሰው እዚያ ሰው ላይ ችግር መፍጠር አይፈልግም። * ኃጢአት የሚያስከትለው በደለኝነት ለዚያ ሰው ሸክም ነው። * “የጌታ ሸክም” የሚለው ምሳሌያዊ አገላለጽ አንድ ነቢይ ለእግዚአብሔር ሕዝብ ያለበትን፣ “የእግዚአብሔር ሸክም” ያመለክታል። * “ሸክም” የተሰኘው ቃል፣ በምንባቡ ዐውድ መሠረት፣ “ኃላፊነት” ወይም፣ “ተግባር” ወይም፣ “መልእክት” ተብሎ ሊተርጎም ይችላል።