am_tw/bible/other/bride.md

7 lines
499 B
Markdown

# ሙሽራ (ሙሽሪት)
ሙሽሪት የወደፊት ባልዋ ከሚሆነው ሙሽራ ጋር ለመጋባት የጋብቻ ሥርዓት ላይ ያለች ሴት ናት።
* ሙሽራ የተሰኘው ቃል በኢየሱስ የሚያምኑ አማኞችን ማለትም ቤተ ክርስቲያንን ለማመልከት ጥቅም ላይ የሚውል ተለዋጭ ዘይቤ ነው።
* ኢየሱስ፣ “የቤተ ክርስቲያን ሙሽራ” በሚል ተለዋጭ ዘይቤ ተጠርቷል።