am_tw/bible/other/bribe.md

1.4 KiB
Raw Permalink Blame History

ጉቦ፣ መማለጃ

“ጉቦ” ወይም መማለጃ፣ ትክክል ወይም ተገቢ ያልሆነ ነገር እንዲያደርግ እዚያ ሰው ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ገንዘብን የመሰለ አንዳች ዋጋ ያለው ነገር መስጠት ማለት ነው።

  • የኢየሱስን ባዶ መቃብር ይጠብቁ የነበሩ ወታደሮች በእርግጥ የሆነውን ነገር እንዳይናገሩ የገንዘብ ጉቦ ተቀብለው ነበር።
  • አንዳንዴ ወንጀልን አይቶ እንዳላየ እንዲያልፍ ወይም አንድ ውሳኔ እንዲያደርግ ለመግንሥት ባለ ሥልጣንም ጉቦ ይሰጣል።
  • ጉቦ መስጠትንም ሆነ መቀበልን መጽሐፍ ቅዱስ ይከለክላል።
  • “ጉቦ” የሚለው ቃል፣ “ተገቢ ያልሆነ ክፍያ” ወይም፣ “ለውሸት የሚደረግ ገንዘብ” ወይም፣ “ሕግን ወይም ደንብን ለመተላለፍ የሚሰጥ ገንዘብ” ተብሎ ሊተርጎም ይችላል።
  • “ጉቦ መስጠት” “አንድ ሰው ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር የሚደረግ ክፍያ” ወይም፣ “ተገቢ ያልሆነ ነገር እንዲደረግ የሚሰጥ ገንዘብ” ወይም፣ “ተወዳጅ ለመሆን ገንዘብ መስጠት” በተሰኘ ቃል ወይም ሐረግ መተርጎም ይችላል።