# ጉቦ፣ መማለጃ “ጉቦ” ወይም መማለጃ፣ ትክክል ወይም ተገቢ ያልሆነ ነገር እንዲያደርግ እዚያ ሰው ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ገንዘብን የመሰለ አንዳች ዋጋ ያለው ነገር መስጠት ማለት ነው። * የኢየሱስን ባዶ መቃብር ይጠብቁ የነበሩ ወታደሮች በእርግጥ የሆነውን ነገር እንዳይናገሩ የገንዘብ ጉቦ ተቀብለው ነበር። * አንዳንዴ ወንጀልን አይቶ እንዳላየ እንዲያልፍ ወይም አንድ ውሳኔ እንዲያደርግ ለመግንሥት ባለ ሥልጣንም ጉቦ ይሰጣል። * ጉቦ መስጠትንም ሆነ መቀበልን መጽሐፍ ቅዱስ ይከለክላል። * “ጉቦ” የሚለው ቃል፣ “ተገቢ ያልሆነ ክፍያ” ወይም፣ “ለውሸት የሚደረግ ገንዘብ” ወይም፣ “ሕግን ወይም ደንብን ለመተላለፍ የሚሰጥ ገንዘብ” ተብሎ ሊተርጎም ይችላል። * “ጉቦ መስጠት” – “አንድ ሰው ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር የሚደረግ ክፍያ” ወይም፣ “ተገቢ ያልሆነ ነገር እንዲደረግ የሚሰጥ ገንዘብ” ወይም፣ “ተወዳጅ ለመሆን ገንዘብ መስጠት” በተሰኘ ቃል ወይም ሐረግ መተርጎም ይችላል።