am_tw/bible/other/bowweapon.md

9 lines
1.2 KiB
Markdown

# ደጋንና ቀስት
ይህ ከደጋን ገመድ ቀስትን ማስፈንጠርን የሚያካትት መሣሪያ ዐይነት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ጠላትን ለማጥቃት ወይም ለምግብ የሚሆን እንስሳን ለመግደል ያገለግል ነበር።
* ደጋን ከእንጨት፣ ክአጥንት፣ ከብረት፣ ወይም የሚዳቋ ቀንድን ከመሳሰሉ ሌሎች ጠንካራ ነገሮች ይሠራል። የጎበጠ ቅርጽ አለው፤ በሲባጎ፣ በገመድ ወይም በጅማት በጥብቅ ይወጠራል።
* ቀስት ጫፉ ላይ ሹል የሆነ ስለታም ዘንግ መሳይ ነገር ነው። በጥንት ዘመን እንጨትን፣ አጥንትን፣ ድንጋይን ወይም ብረትን ከመሳሰሉ የተለያዩ ነገሮች ቀስት ይሠራ ነበር።
* አዳኞችና ጦረኞች ሁሉ በደጋንና በቀስት ይጠቀሙ ነበር።
* “ቀስት” የተሰኘው ቃል አንዳንድ የጠላትን ጥቃት ወይም መለኮታዊ ፍርድን ለማመልከት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምሳሌያዊ በሆነ አነጋገር ጥቅም ላይ ይውል ነበር።