11 lines
1.6 KiB
Markdown
11 lines
1.6 KiB
Markdown
# ማጎንበስ፣ ጎንበስ ማለት
|
|
|
|
ማጎንበስ ለአንድ ሰው ክብርን ለማሳየት በትሕትና ከወገብ እጥፍ ማለት ነው። “ጎንበስ ማለት” በጣም መታጠፍ ወይም በጣም ዝቅ ብሎ መንበርከክ ማለት ሲሆን፣ ብዙውን ጊዜ ግንባርንና እጆችን መሬት ላይ ማድረግንም ይጨምራል።
|
|
|
|
* ሌሎች ገለጻዎች፣ “ጉልበትን ማጠፍ” (ማለት መንበርከክ)፣ “ራስን ዝቅ ማድረግ” (ማለት አክብሮትን ወይም ሐዘንን ለማሳየት ራስን በትሕትና ወደ ፊት ዘንበል ማለትን) ይጨምራል።
|
|
* ጎንበስ ማለት የጭንቀት ወይም የሐዘን ምልክትም ይሆናል። በጣም “ጎንበስ ያለ” ሰው ወደ መጨረሻ የዝቅተኝነት ደረጃ ወርዷል ማለት ነው።
|
|
* አንድ ሰው ነገሥታትንና ሌሎች መሪዎችን በመሳሰሉ ከፍ ያለ ደረጃ ወይም ከፍ ያለ ሥልጣን ባላቸው ሰዎች ፊት ሲቀርብ ብዙውን ጊዜ ጎንበስ ይላል።
|
|
* በእግዚአብሔር ፊት ማጎንበስ እርሱን የማምለክ መገለጫ ነው።
|
|
* ከተአምራቱና ከትምህርቱ የተነሣ እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣ መሆኑን ሰዎች ሲገነዘቡ ኢየሱስ ፊት ማጎንበሳቸውን መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
|
|
* መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን አንድ ቀን ኢየሱስ ሲመጣ ሰዎች ሁሉ እርሱን ለማምለክ ይንበረከካሉ።
|