am_tw/bible/other/bow.md

1.6 KiB

ማጎንበስ፣ ጎንበስ ማለት

ማጎንበስ ለአንድ ሰው ክብርን ለማሳየት በትሕትና ከወገብ እጥፍ ማለት ነው። “ጎንበስ ማለት” በጣም መታጠፍ ወይም በጣም ዝቅ ብሎ መንበርከክ ማለት ሲሆን፣ ብዙውን ጊዜ ግንባርንና እጆችን መሬት ላይ ማድረግንም ይጨምራል።

  • ሌሎች ገለጻዎች፣ “ጉልበትን ማጠፍ” (ማለት መንበርከክ)፣ “ራስን ዝቅ ማድረግ” (ማለት አክብሮትን ወይም ሐዘንን ለማሳየት ራስን በትሕትና ወደ ፊት ዘንበል ማለትን) ይጨምራል።
  • ጎንበስ ማለት የጭንቀት ወይም የሐዘን ምልክትም ይሆናል። በጣም “ጎንበስ ያለ” ሰው ወደ መጨረሻ የዝቅተኝነት ደረጃ ወርዷል ማለት ነው።
  • አንድ ሰው ነገሥታትንና ሌሎች መሪዎችን በመሳሰሉ ከፍ ያለ ደረጃ ወይም ከፍ ያለ ሥልጣን ባላቸው ሰዎች ፊት ሲቀርብ ብዙውን ጊዜ ጎንበስ ይላል።
  • በእግዚአብሔር ፊት ማጎንበስ እርሱን የማምለክ መገለጫ ነው።
  • ከተአምራቱና ከትምህርቱ የተነሣ እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣ መሆኑን ሰዎች ሲገነዘቡ ኢየሱስ ፊት ማጎንበሳቸውን መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
  • መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን አንድ ቀን ኢየሱስ ሲመጣ ሰዎች ሁሉ እርሱን ለማምለክ ይንበረከካሉ።