1.1 KiB
1.1 KiB
ዘካርያስ (ብሉይ ኪዳን)
ብሉይ ኪዳን ውስጥ ዘካርያስ ተብለው የተጠሩ ብዙ ሰዎች ነበሩ። ከእነርሱም ዋና ዋናዎቹ፣
- በንጉሥ ዳዊት ዘመን የነበረው ታዋቂ የቤተ መቅደሱ በር ጠባቂ (1ዜና 26፡2፣14)።
- ኢዮራም የተባለው ወንድሙ የገደለው የንጉሥ ኢዮሳፍጥ ልጅ (2ዜና 21፡2)።
- ጣዖት በማምለካቸው ስለ ገሠፃቸው ሕዝቡ በድንጋይ ቀጥቅጠው የገደሉት ካህን (2ዜና 24፡20)።
- ለስድስት ወር ብቻ ሥልጣን ላይ ከቀየ በኋላ የተገደለው የእስራኤል ንጉሥ (2ነገሥት 14፡29)።
- በንጉሥ ዳርዮስ ቀዳማዊ ዘመን ትንቢት የተናገረ ነቢይ። የእርሱ ትንቢት የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት እየተመለሱ የነበሩ ምርኮኞችን ያበረታታ ነበር። እርሱ የነበረው ዕዝራ፣ ነህምያ፣ ዘሩባቤልና ነቢዩ ሐጌ በነበሩበት ዘመን ነበር።