ዑር
ዑር በጥንቱ ከለድያ አካባቢ ኤፍራጥስ ወንዝ ዳር የነበረ ጠቃሚ ከተማ ሲሆን የሚገኘው በዚህ ዘመን ኢራቅ በሚባለው አገር ውስጥ ነው።
- አብርሃም የመጣው ከዑር ነበር፤ ወደ ምድረ ከነዓን እንዲሄድ እግዚአብሔር የጠራው ከዚያ ነበር።
- የአብርሃም ወንድምና የሎጥ አባት ሐራን የሞተው በዑር ነበር። ምናልባትም ዑርን ለቅቆ በወጣ ጊዜ ሎጥ ከአብርሃም ጋር እንዲሄድ ምክንያት የሆነው ይህ ሊሆን ይችላል።