894 B
894 B
ስምዖን
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስምዖን የተባሉ ጥቂት ሰዎች ነበሩ
- ብሉይ ኪዳን ውስጥ የያዕቆብ (እስራኤል) እና የልያ ሁለተኛ ልጅ ስምዖን ይባል ነበር። የእርሱ ዘሮች ከአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች አንዱ ሆኗል።
- የስምዖን ነገድ የከነዓንን ደቡባዊ ጫፍ፣ ማለትም የይሁዳ ርስት ክፍል የነበረውን አካባቢ ይዞ ነበር
- ማርያምና ዮሴፍ ሕፃን ኢየሱስን ለእግዚአብሔር ለመስጠት ወደዚያ ባመጡት ጊዜ ስምዖን የሚባል ፃድቅ ሰው በኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ ነበር ስምዖን ኢየሱስን ባረከ፤ የሰዎች ሁሉ አዳኝ የሚሆነውን መሲሕ በመስጠቱም እግዚአብሔርን አመሰገነ