am_tw/bible/names/korah.md

8 lines
680 B
Markdown

# ቆሬ
ብሉይ ኪዳን ውስጥ ቆሬ በትንሹ የሁለት ሰዎች ስም ነው።
* ከኤሳው ልጆች አንዱ ቆሬ ይባል ነበር። እርሱም ይኖርበት ለነበረው ማኅበረ ሰብ መሪ ይሆናል።
* ሌላው ቆሬ የሌዊ ዘር ሲሆን፣ ካህን ሆኖ መገናኛው ድንኳን ውስጥ አገልግሏል። እግዚአብሔር ለሙሴና ለአሮን በሰጠው ስፍራና ሥልጣን ቅናት አድሮበት ነበር።
* የእስራኤላን ሕዝብ እግዚአብሔር በሰጣቸው መሪዎች ላይ ለማሳመፅ ከድታንና ከአቤሮን ጋር ሲያሤር ነበር።