am_tw/bible/names/kedar.md

8 lines
888 B
Markdown

# ቄዳር
ቄዳር የእስማኤል ሁለተኛ ልጅ ሲሆን፣ ከእርሱ ዘሮች ብዙ ሕዝብ ያለው ነበር። ቄዳር የምትባል ታውቂ ከተማም አለች።
* የቄዳር ከተማ የምትገኘው በአረቢያ ሰሜናዊ ክፍል ከፓለስቲና ደቡባዊ ድንበር በኩል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን በትልቅነቷና በውበቷ ትታወቅ ነበር።
* “ጥቋቁሮቹ የቄዳር ድንኳኖች” የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው የቄዳር ሕዝብ ይኖሩበት የነበረውን ከጥቋቁር የፍየል ቆዳ የተሠራውን ድንኳናቸውን ነው።
* መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “የቄዳር ክብር” የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው የዚያችን ከተማ ሕዝብ ታላቅነት ነው።