769 B
769 B
ኢዮጴ
መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ኢዮጴ ከተማ ከኢየሩሳሌም ሰሜናዊ ምዕራብ 30 ማይሎች ርቃ ሜድትራንያን ባሕር ላይ የምትገኝ በጣም ጠቃሚ የንግድ ባሕር ወደብ ነበረች።
- ጥንት ኢዮጴ የነበረችበት ቦታ በዚህ ዘመን ጃፋ ከተማ ያለችበት ሲሆን፣ ጃፋ ቤቴል አቪብ ከተማ አካል ነት።
- ብሉይ ኪዳን እንደሚነግረን ዮናስ ወደተርሴስ የሚሄድ መርከብ የተሳፈረው ከኢዮጴ ነበር።
- አዲስ ኪዳን እንደሚነግረን ጴጥሮስ ጣቢታ የምትባለውን ክርስቲያን ልጅ ከሞት ያስነሣው ኢዮጴ ነበር።