am_tw/bible/names/jerusalem.md

14 lines
2.0 KiB
Markdown

# ኢየሩሳሌም
ኢየሩሳሌም በኋላ እጅግ ተፈላጊ የሆነች በመጀመሪያ የከነዓናውያን የነበረች ጥንታዊት ከተማ ነበረች። አሁንም ኢየሩሳሌም የዘመናዊት ኢየሩሳሌም ዋና ከተማ ነች።
* የብሉይ ኪዳንዋ የሳሌም ከተማ ምናልባት የአሁኗ ኢየሩሳሌም ከተማ ሳትሆን እንዳልቀረች ይታሰባል። ሁለቱም ስሞች፣ “ሰላም” የሚል ትርጉም ያለው ሥርወ ቃል አላቸው።
* አብርሃም የኢየሩሳሌም ከተማ አካል በሆነው በሞሪያ ተራራ ልጁ ይስሐቅን መሥዋዕት አቀረበ።
* ንጉሥ ዳዊት ከኢያቡሳውያን ነጥቆ ኢየሩሳሌምን ያዘ፤ ዋና ከተማዋም አደረጋት።
* የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በኢየሩሳሌም ያለ ሞሪያ ተራራ ላይ የመጀመሪያውን ቤተመቅደስ ሠራ።
* ባቢሎናውያን ኢየሩሳሌምን ደመሰሱ፤ ከ70 ዓመት በኋላ ግን ተመልሰው ከተማዋን እንዲሠሩ እግዚአብሔር ፈቀደላቸው።
* ቤተመቅደሱ የነበረው እዚያ በመሆኑ፣ ዋና ዋናዎቹ የአይሁድ በዓሎች የሚከበሩበት ማዕከል ኢየሩሳሌም ነበረች።
* ኢየሱስ በሕፃንነቱ ለእግዚአብሔር የተሰጠው ኢየሩሳሌም በነበረው ቤተመቅደስ ነበር። ለፍርድ የቀረበውና መስቀል ላይ እንዲሞት የተፈረደበትም በኢየሩሳሌም ነበር።
* ኢየሱስ ከሞት ከተነሣ በኋላ ወደ ሰማይ ከመመለሱ በፊት ከደቀመዛሙርቱ ጋር ጊዜ ካሳለፈባቸው ዋና ዋና ቦታዎች አንዷ ኢየሩሳሌም ነበረች።
* ኢየሩሳሌም ያለችው በእስራኤል ተራሮች ላይ በመሆኑ ወደኢየሩሳሌም የሚሄዱ ሰዎች፣ “ወደ ኢየሩሳሌም እየወጣን ነው” ይሉ ነበር።