am_tw/bible/names/jehu.md

9 lines
686 B
Markdown

# ኢዩ
ብሉይ ኪዳን ውስጥ ኢዩ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ሰዎች አሉ።
* አንደኛው ኢዩ በእስራኤል ንጉሥ በአክዓብና በይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ዘመን የነበረ ነብይ ነው።
* ንጉሥ ሆኖ ለሃያ ስምንት ዓመት ይሁዳን የገዛ ኢዩ የሚባል የጦር መሪ ነበር።
* ኢዩ ክፉዋ ንግሥት ኤልዛቤልን ጨምሮ የቀድሞው ንጉሥ አክዓብ ዘመዶችን ሁሉ ገደለ።
* ከአክዓብ ጋር ዝምድና የነበራቸው ሁለት ንጉሦችንም ገድሏል፤ የእስራኤል ኢዮራምና የይሁዳ አሃዝያ።