am_tw/bible/names/goliath.md

8 lines
761 B
Markdown

# ጎልያድ
ጎልያድ ዳዊት በወንጭፍ ድንጋይ የገደለው ግዙፍ ፍልስጥኤማዊ ወታደር ነበር።
* ጎልያድ ከሁለት እስከ ሦስት ሜትር ይረዝም ነበር። በጣም ትልቅ ከመሆኑ የተነሣ ብዙውን ጊዜ ጊዜ ግዙፍ ሰው እየተባለ ይጠራል።
* ምንም እንኳ ጎልያድ የበለጠ መሣሪያ ቢኖረውም፣ ከዳዊት የበለጠ ግዙፍ ቢሆንም፣ እግዚአብሔር ለዳዊት ጎልያድን የሚያሸንፍበትን ብርታትና ችሎታ ሰጠው።
* ዳዊት ጎልያድን ድል ከማድረጉ የተነሣ እስራኤላውያን ፍልስጥኤማውያንን ድል እንዳደረጉ ተቆጠረ።