# ጎልያድ ጎልያድ ዳዊት በወንጭፍ ድንጋይ የገደለው ግዙፍ ፍልስጥኤማዊ ወታደር ነበር። * ጎልያድ ከሁለት እስከ ሦስት ሜትር ይረዝም ነበር። በጣም ትልቅ ከመሆኑ የተነሣ ብዙውን ጊዜ ጊዜ ግዙፍ ሰው እየተባለ ይጠራል። * ምንም እንኳ ጎልያድ የበለጠ መሣሪያ ቢኖረውም፣ ከዳዊት የበለጠ ግዙፍ ቢሆንም፣ እግዚአብሔር ለዳዊት ጎልያድን የሚያሸንፍበትን ብርታትና ችሎታ ሰጠው። * ዳዊት ጎልያድን ድል ከማድረጉ የተነሣ እስራኤላውያን ፍልስጥኤማውያንን ድል እንዳደረጉ ተቆጠረ።