am_tw/bible/names/elizabeth.md

8 lines
585 B
Markdown

# ኤልሳቤጥ
ኤልሳቤጥ የመጥምቁ ዮሐንስ እናት ናት። የባልዋ ስም ዘካርያስ ነበር።
* ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ አልነበራቸውም፤ በስተርጅናቸው ግን ወንድ ልጅ እንደሚወልዱ እግዚአብሔር ቃል ገባላቸው።
* እግዚአብሔር ቃሉን ጠበቀ፤ ብዙም ሳይቆይ ኤልሳቤጥ ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች። ሕፃኑንም ዮሐንስ አሉት።
* ኤልሳቤጥ የኢየሱስ እናት የማርያምም ዘመድ ነበረች።