am_tw/bible/names/capernaum.md

9 lines
837 B
Markdown

# ቅፍርናሆም
ቅፍርናሆም ከገሊላ ባሕር ዳርቻ ሰሜን ምዕራብ የምትገኝ ዓሣ የሚጠመድባት ቦታ ናት።
* ገሊላ ውስጥበሚያስተምርበት ጊዜ ኢየሱስ ይኖር የነበረው በቅፍርናሆም ነበር።
* ከደቀ መዛሙርቱ ጥቂቶቹ ከቅፍርናሆም የመጡ ነበር።
* የሞተችውን ልጅ ማስነሣትን ጨምሮ ኢየሱስ በዚህች ከተማ ብዙ ተአምራት አድርጎ ነበር።
* ሕዝቦቿ እርሱን ችላ በማለታቸውና መልእክቱንም ባለማመናቸው ኢየሱስ ከገሰጻቸው ሦስት ከተሞች አንኳ ቅፍርናሆም ናት። ባለ ማመናቸው ምክንያት እግዚአብሔር እንደሚቀጣቸው አስጠንቅቋቸው ነበር።