am_tw/bible/names/caesar.md

11 lines
1.5 KiB
Markdown

# ቄሳር
“ቄሳር” የተሰኘው ቃል ብዙዎቹ የሮም ገዦች የሚጠቀሙበት ስም ወይም መጠሪያ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይህ መጠሪያ ሦስት ገዦችን ያመለክታል።
* ቄሳር ተብሎ የተጠራ የመጀመሪያ ሮማዊ መሪ ኢየሱስ በተወለደበት ዘመን ሲገዛ የነበረው፣ “አውጉስጦስ ቄሳር” ነው።
* ከሰላሳ ዓመት በኋላ ዮሐንስ እየሰበከ በነበረበት ዘመን የሮም መንግሥትን ይገዛ የነበረው ጤባርዮስ ቄሳር ነበር።
* የቄሳርን ለቄሳር፣ የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር መስጠት እንደሚገባ ኢየሱስ ለሕዝቡ በተናገረ ጊዜ ጤባርዮስ ቄሳር ሮምን እየገዛ ነበር።
* ጳውሎስ ቄሳር ፊት ቀርቦ እንደ ነበር ሲናገር የሚያመለክተው ኔሮ የተባለውን ሮማዊ ንጉሥ ሲሆን፣ እርሱም፣ “ቄሳር” በተሰኘው መጠሪያ ነበር የሚታወቀው።
* “ቄሳር” የተሰኘው ቃል እንደ መጠሪያ ብቻውን ጥቅም ላይ ከዋለ፣ “ንጉሥ” ወይም፣ “ሮማዊ ገዢ” ተብሎ መተርጎም ይችላል።
* አውጉስጦስ ቄሳር ወይም ጤባርዮስ ቄሳር በተሰኙት ስሞች “ቄሳር” የሚለው ቃል ለአገሬው ሕዝብ ቋንቋ በሚቀራረብ ቋንቋ መነገር ይችላል።