# ቄሳር “ቄሳር” የተሰኘው ቃል ብዙዎቹ የሮም ገዦች የሚጠቀሙበት ስም ወይም መጠሪያ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይህ መጠሪያ ሦስት ገዦችን ያመለክታል። * ቄሳር ተብሎ የተጠራ የመጀመሪያ ሮማዊ መሪ ኢየሱስ በተወለደበት ዘመን ሲገዛ የነበረው፣ “አውጉስጦስ ቄሳር” ነው። * ከሰላሳ ዓመት በኋላ ዮሐንስ እየሰበከ በነበረበት ዘመን የሮም መንግሥትን ይገዛ የነበረው ጤባርዮስ ቄሳር ነበር። * የቄሳርን ለቄሳር፣ የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር መስጠት እንደሚገባ ኢየሱስ ለሕዝቡ በተናገረ ጊዜ ጤባርዮስ ቄሳር ሮምን እየገዛ ነበር። * ጳውሎስ ቄሳር ፊት ቀርቦ እንደ ነበር ሲናገር የሚያመለክተው ኔሮ የተባለውን ሮማዊ ንጉሥ ሲሆን፣ እርሱም፣ “ቄሳር” በተሰኘው መጠሪያ ነበር የሚታወቀው። * “ቄሳር” የተሰኘው ቃል እንደ መጠሪያ ብቻውን ጥቅም ላይ ከዋለ፣ “ንጉሥ” ወይም፣ “ሮማዊ ገዢ” ተብሎ መተርጎም ይችላል። * አውጉስጦስ ቄሳር ወይም ጤባርዮስ ቄሳር በተሰኙት ስሞች “ቄሳር” የሚለው ቃል ለአገሬው ሕዝብ ቋንቋ በሚቀራረብ ቋንቋ መነገር ይችላል።