am_tw/bible/names/babel.md

9 lines
1.2 KiB
Markdown

# ባቤል
ባቤል ከመሰጵጦምያ በስተደቡብ በነበረችው ሰናዖር በምትባል አካባቢ ዋነኛ ከተማ ነበረች በኋላ ላይ ሰናዖር ባቢሎን ተብላለች
* የባቢሎን ከተማ የተመሠረተችው የሰናዖር አካባቢን ከገዛው የካም የልጅ ልጅ በነበረው በናምሩድ ነበር
* የሰናዖር ሕዝብ በጣም ትዕቢተኞች ከመሆናቸው የተነሳ ወደሰማይ የሚደርስ ግንብ መሥራት ሞከሩ። በኋላ ላይ ይህ፥ “የባቢሎን ግንብ” በመባል የሚታወቅ ሆነ
* ግንቡን እየሰሩ የነበሩ ሰዎች እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ባለመበተናቸው እርስ በርስ መግባባት እንዳይችሉ ቋንቋቸውን ደበላለቀው። ይህም ከዚያ ተነስተው በተለያዩ የምድር አካባቢዎች እንዲኖሩ አደረጋቸው።
* “ባቤል” የተሰኘው ቃል ትርጉም ሥረ-መሠረት፥ “ግራ መጋባት” ማለት ሲሆን እንዲህ የተባለው እግዚአብሔር የሕዝቡን ቋንቋ ስለደበላለቀው ነው።