# ባቤል ባቤል ከመሰጵጦምያ በስተደቡብ በነበረችው ሰናዖር በምትባል አካባቢ ዋነኛ ከተማ ነበረች በኋላ ላይ ሰናዖር ባቢሎን ተብላለች * የባቢሎን ከተማ የተመሠረተችው የሰናዖር አካባቢን ከገዛው የካም የልጅ ልጅ በነበረው በናምሩድ ነበር * የሰናዖር ሕዝብ በጣም ትዕቢተኞች ከመሆናቸው የተነሳ ወደሰማይ የሚደርስ ግንብ መሥራት ሞከሩ። በኋላ ላይ ይህ፥ “የባቢሎን ግንብ” በመባል የሚታወቅ ሆነ * ግንቡን እየሰሩ የነበሩ ሰዎች እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ባለመበተናቸው እርስ በርስ መግባባት እንዳይችሉ ቋንቋቸውን ደበላለቀው። ይህም ከዚያ ተነስተው በተለያዩ የምድር አካባቢዎች እንዲኖሩ አደረጋቸው። * “ባቤል” የተሰኘው ቃል ትርጉም ሥረ-መሠረት፥ “ግራ መጋባት” ማለት ሲሆን እንዲህ የተባለው እግዚአብሔር የሕዝቡን ቋንቋ ስለደበላለቀው ነው።