am_tw/bible/kt/zealous.md

955 B

ቅንዓት፣ ቀናተኛ (ቀናዒ)

“ቅንዓት” እና፣ “ቀናተኛ” የአንድ ሰው ወይም ሐሰብ ጠንካራ ደጋፊ መሆንን ያመለክታል።

  • ቅንዓት መልካም ዓላምን ለመፈጸም የሚኖር ጠንካራ ፍላጎትና ሥራንም ይጨምራል። በታማኝነት ለእግዚአብሔር የሚታዘዝና ሌሎችም ያኑ እንዲያደርጉ የሚያስተምር ሰውን ለማመልከትም ጥቅም ላይ ይውላል።
  • ቀናዒነት አንድን ነገር ለማድረግ ከፍ ያለ ጥረት ማድረግንና በዚያ ጥረት መጽናትንም ያካትታል።
  • “የጌታ ቅንዓት” ወይም፣ “የያህዌ ቅንዓት” የምኪያመለክተው ሕዝቡን ለመባረክና ፍትሕ ሰፍኖ ለማየት የእግዚአብሔር የሚወሰደውን ጠንካራና ያልተቆጠበ ርምጃ ያመለክታል።