am_tw/bible/kt/zealous.md

8 lines
955 B
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ቅንዓት፣ ቀናተኛ (ቀናዒ)
“ቅንዓት” እና፣ “ቀናተኛ” የአንድ ሰው ወይም ሐሰብ ጠንካራ ደጋፊ መሆንን ያመለክታል።
* ቅንዓት መልካም ዓላምን ለመፈጸም የሚኖር ጠንካራ ፍላጎትና ሥራንም ይጨምራል። በታማኝነት ለእግዚአብሔር የሚታዘዝና ሌሎችም ያኑ እንዲያደርጉ የሚያስተምር ሰውን ለማመልከትም ጥቅም ላይ ይውላል።
* ቀናዒነት አንድን ነገር ለማድረግ ከፍ ያለ ጥረት ማድረግንና በዚያ ጥረት መጽናትንም ያካትታል።
* “የጌታ ቅንዓት” ወይም፣ “የያህዌ ቅንዓት” የምኪያመለክተው ሕዝቡን ለመባረክና ፍትሕ ሰፍኖ ለማየት የእግዚአብሔር የሚወሰደውን ጠንካራና ያልተቆጠበ ርምጃ ያመለክታል።