ማምለክ፣ መስገድ
“ማምለክ፣ መስገድ” እግዚአብሔርን ማክበር፣ ማመስገንና ለእርሱ መታዘዝ ማለት ነው።
- ቃል በቃል ከተወሰደ፣ “በጣም ማጎንበስ” ወይም፣ በትሕትና እርሱን ለማክበር እፊቱ መደፋት ማለት ነው።
- እርሱን በማመስገንና በመታዘዝ እርሱን ስናገለግልና ስናከብር እግዚአብሔርን ማክበራችን ነው።
- እስራኤላውያን እግዚአብሔርን ሲያመልኩ አብዛኛውን ጊዜ መሠዊያው ላይ መሥዋዕት ያቀርቡ ነበር።
- አንዳንዶች ሐሰተኛ አማልክት ያመልካሉ።