am_tw/bible/kt/thetwelve.md

929 B

አሥራ ሁለቱ፣ አሥራ አንዱ

“አሥራ ሁለቱ” የቅርብ ደቀ መዛሙርቱ ወይም ሐዋርያቱ እንደሆኑ ኢየሱስ የመረጣቸው አሥራ ሁለት ሰዎች ናቸው። ይሁዳ ራሱን ከገደለ በኋላ፣ “አሥራ አንዱ ቀሩ።

  • ኢየሱስ ሌሎች ብዙ ደቀ መዛሙርትም ነበሩት፤ “አሥራ ሁለቱ” ግን በሦስት ዓመት ተኩል አገልግሎቱ እስከ መጨረሻው የተከተሉት ናቸው።
  • የእነዚህ አሥራ ሁለት ደቀ መዛሙርት ስም ማቴዎስ 10፣ ማርቆስ 3 እና ሉቃስ 6 ላይ ተዘርዝሮአል።
  • ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከተመለሰ በኋላ “አሥራ አንዱ” የይሁዳን ቦታ እንዲይዝ ማትያስ የተባለ ደቀ መዝሙር መረጡ። ከዚያም እንደ ገና፣ “አሥራ ሁለቱ” ተባሉ።