am_tw/bible/kt/tempt.md

1.1 KiB

መፈተን፣ ፈተና

መፈተን አንድ ሰው ተገቢ ያልሆነ ነገር እንዲያደርግ መሞከር ማለት ነው።

  • ፈተና የሚባለው አንድ ሰው ተገቢ ያልሆነ ነገር ለማድረግ እንዲፈልግ ማድረግ ነው።
  • ሰዎች በራሳቸው ኀጥእ ባሕርይና በሌሎች ይፈተናሉ።
  • ለእግዚአብሔር ባለ መታዘዝና መጥፎ ነገሮችን በማድረግ እግዚአብሔር ላይ ኀጢአት እንዲሠሩ ሰይጣንም ሰዎችን ይፈትናል።
  • ሰይጣን ኢየሱስን ፈተነው፤ ተገቢ ያልሆነ ነገር ሊያስደርገውም ሞከረ፤ ኢየሱስ ግን የሰይጣንን ፈተናዎች ሁሉ ተቋቋመ፤ ኀጢአትም አላደረገም።
  • “መፈተን” የሚለው ቃል እግዚአብሔር መፈተን ለማለትም ጥቅም ላይ ይውላል፤ ይህም አልታዘዝ ባዩን በመቅጣት ምላሽ እስኪሰጥ ድረስ በእግዚአብሔር ላይ በማመጽ መጽናት ማለት ነው። ይህ ሁኔታ እግዚአብሔርን መፈታተን ይባላል።