am_tw/bible/kt/tempt.md

10 lines
1.1 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# መፈተን፣ ፈተና
መፈተን አንድ ሰው ተገቢ ያልሆነ ነገር እንዲያደርግ መሞከር ማለት ነው።
* ፈተና የሚባለው አንድ ሰው ተገቢ ያልሆነ ነገር ለማድረግ እንዲፈልግ ማድረግ ነው።
* ሰዎች በራሳቸው ኀጥእ ባሕርይና በሌሎች ይፈተናሉ።
* ለእግዚአብሔር ባለ መታዘዝና መጥፎ ነገሮችን በማድረግ እግዚአብሔር ላይ ኀጢአት እንዲሠሩ ሰይጣንም ሰዎችን ይፈትናል።
* ሰይጣን ኢየሱስን ፈተነው፤ ተገቢ ያልሆነ ነገር ሊያስደርገውም ሞከረ፤ ኢየሱስ ግን የሰይጣንን ፈተናዎች ሁሉ ተቋቋመ፤ ኀጢአትም አላደረገም።
* “መፈተን” የሚለው ቃል እግዚአብሔር መፈተን ለማለትም ጥቅም ላይ ይውላል፤ ይህም አልታዘዝ ባዩን በመቅጣት ምላሽ እስኪሰጥ ድረስ በእግዚአብሔር ላይ በማመጽ መጽናት ማለት ነው። ይህ ሁኔታ እግዚአብሔርን መፈታተን ይባላል።