am_tw/bible/kt/spirit.md

1.5 KiB

መንፈስ፥ መንፈሳዊ

“መንፈስ” የሚለው ቃል የሰዎችን ቁሳዊ ያልሆነና የማይታይ ክፍል ያመለክታል። ሰው ሲሞት መንፈሱ ከአካሉ ይለያያል

  • “መንፈስ” ቁሳዊ አካል የሌለውን በተለይ መልካም ወይም ክፉ መናፍስትን ሊያመለክት ይችላል
  • የሰው መንፈስ እግዚአብሔርን የሚያውቅበትና በእርሱ የሚያምንመበት ክፍል ነው
  • በአጠቃላይ፣ “መንፈሳዊ” ቁሳዊ ያልሆነ ዓለም ማንኛውም ክፍል ነው
  • በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት፣ “መንፈሳዊ” ከእግዚአብሔር ጋር ሚያያዝ ማንኛውንም ነገር በተለይም፣ መንፈስ ቅዱስን ያመለክታል
  • ለምሳሌ፣ “መንፈሳዊ ምግብ” የሰውን መንፈስ የሚመግብ የእግዚአብሔር ትምህርት ሲያመለክት፣ “መንፈሳዊ ጥበብ” ከመንፈስ ቅዱስ ኅይል የሚገኝ ዕውቀትና መልካም አኗኗር ያመለክታል
  • እግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ ቁሳዊ አካል የሌላቸው መንፈሳዊ ፍጡራንን የፈጠረም እርሱ ነው
  • በእግዚአብሔር ያመፁትንና ክፉ መናፍስት የሆኑትን ጨምሮ መላእክት መንፈሳዊ ፍጡራን ናቸው
  • “የ. . .መንፈስ” ከተባለ፣ “የጥበብ መንፈስን” ጨምሮ፣ “የ. . . መንፈስ” ባሕርይ ሲኖር ማለት ነው