am_tw/bible/kt/spirit.md

13 lines
1.5 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# መንፈስ፥ መንፈሳዊ
“መንፈስ” የሚለው ቃል የሰዎችን ቁሳዊ ያልሆነና የማይታይ ክፍል ያመለክታል። ሰው ሲሞት መንፈሱ ከአካሉ ይለያያል
* “መንፈስ” ቁሳዊ አካል የሌለውን በተለይ መልካም ወይም ክፉ መናፍስትን ሊያመለክት ይችላል
* የሰው መንፈስ እግዚአብሔርን የሚያውቅበትና በእርሱ የሚያምንመበት ክፍል ነው
* በአጠቃላይ፣ “መንፈሳዊ” ቁሳዊ ያልሆነ ዓለም ማንኛውም ክፍል ነው
* በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት፣ “መንፈሳዊ” ከእግዚአብሔር ጋር ሚያያዝ ማንኛውንም ነገር በተለይም፣ መንፈስ ቅዱስን ያመለክታል
* ለምሳሌ፣ “መንፈሳዊ ምግብ” የሰውን መንፈስ የሚመግብ የእግዚአብሔር ትምህርት ሲያመለክት፣ “መንፈሳዊ ጥበብ” ከመንፈስ ቅዱስ ኅይል የሚገኝ ዕውቀትና መልካም አኗኗር ያመለክታል
* እግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ ቁሳዊ አካል የሌላቸው መንፈሳዊ ፍጡራንን የፈጠረም እርሱ ነው
* በእግዚአብሔር ያመፁትንና ክፉ መናፍስት የሆኑትን ጨምሮ መላእክት መንፈሳዊ ፍጡራን ናቸው
* “የ. . .መንፈስ” ከተባለ፣ “የጥበብ መንፈስን” ጨምሮ፣ “የ. . . መንፈስ” ባሕርይ ሲኖር ማለት ነው