am_tw/bible/kt/sonofman.md

13 lines
1.3 KiB
Markdown

# የሰው ልጅ
የሰው ልጅ“የሰው ልጅ” የሚለው ሐረግ ብዙ ጊዜ ኢየሱስ ራሱን የሚጠራበት ስም ነበር። ብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ “የሰው ልጅ” ማንኛውም ሰው የሚታወቅበት ስም ነበር
* ብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ “የሰው ልጅ” የተሰኘው ሐረግ ብዙውን ጊዜ፣ “ሰው” ወይም “ሰብዓዊ ፍጡር” ለማለት ጥቅም ላይ ይውል ነበር
* ከትንቢተ ሕዝቅኤል እንደምንመለከተው እግዚአብሔር ነቢዩን፣ “የሰው ልጅ” በማለት ጠርቶታል። ለምሳሌ፣ “የሰው ልጅ ሆይ ትንቢት ተናገር” እንደሚለው
* “እኔ” ከማለት ይልቅ ኢየሱስ ራሱን በዚህ ቃል ይጠራ ነበር
* ነቢዩ ዳንኤል በራእዩ፣ “የሰው ልጅ” ከደመና ጋር ሲመጣ አይቶ ነበር። ይህ የሚያመለክተው የመሲሑን መምጣት ነበር
* ኢየሱስ ስለ ራሱ ሲናገር፣ አንድ ቀን “የሰው ልጅ” በደመና ተመልሶ ይመጣል አለ
* ኢየሱስ በደመና እንደሚመጣ የሚናገሩት እነዚህ
ጥቅሶች እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን ያመለክታሉ