am_tw/bible/kt/sonofman.md

1.3 KiB

የሰው ልጅ

የሰው ልጅ“የሰው ልጅ” የሚለው ሐረግ ብዙ ጊዜ ኢየሱስ ራሱን የሚጠራበት ስም ነበር። ብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ “የሰው ልጅ” ማንኛውም ሰው የሚታወቅበት ስም ነበር

  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ “የሰው ልጅ” የተሰኘው ሐረግ ብዙውን ጊዜ፣ “ሰው” ወይም “ሰብዓዊ ፍጡር” ለማለት ጥቅም ላይ ይውል ነበር
  • ከትንቢተ ሕዝቅኤል እንደምንመለከተው እግዚአብሔር ነቢዩን፣ “የሰው ልጅ” በማለት ጠርቶታል። ለምሳሌ፣ “የሰው ልጅ ሆይ ትንቢት ተናገር” እንደሚለው
  • “እኔ” ከማለት ይልቅ ኢየሱስ ራሱን በዚህ ቃል ይጠራ ነበር
  • ነቢዩ ዳንኤል በራእዩ፣ “የሰው ልጅ” ከደመና ጋር ሲመጣ አይቶ ነበር። ይህ የሚያመለክተው የመሲሑን መምጣት ነበር
  • ኢየሱስ ስለ ራሱ ሲናገር፣ አንድ ቀን “የሰው ልጅ” በደመና ተመልሶ ይመጣል አለ
  • ኢየሱስ በደመና እንደሚመጣ የሚናገሩት እነዚህ

ጥቅሶች እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን ያመለክታሉ