am_tw/bible/kt/sonofgod.md

10 lines
943 B
Markdown

# የእግዚአብሔር ልጅ፣ ልጁ፣ ልጅ(ወልድ)
“የእግዚአብሔር ልጅ” ሰው ሆኖ ወደ ዓለም የመጣውን ቃል ኢየሱስን ያመለክታል። ብዙውን ጊዜ፣ “ልጁ” ተብሎም ይጠራል
* የእግዚአብሔር ልጅ የእግዚአብሔር ባሕርያት አሉት፤ እርሱ ፍጹም እግዚአብሔር ነው
* እግዚአብሔር አብ፣ እግዚአብሔር ወልድና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሦስቱም በባሕርይ አንድ ናቸው
* ከሰው ልጆች በተለየ መልኩ የእግዚአብሔር ልጅ ለዘላለም ነበር
* በመጀመሪያ የእግዚአብሔር ልጅ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ዓለምን ፈጥሯል
* ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ በመሆኑ፣ አባቱን ይወዳል፤ ለአባቱም ይታዘዛል፤ አባቱም ይወደዋል