am_tw/bible/kt/sonofgod.md

943 B

የእግዚአብሔር ልጅ፣ ልጁ፣ ልጅ(ወልድ)

“የእግዚአብሔር ልጅ” ሰው ሆኖ ወደ ዓለም የመጣውን ቃል ኢየሱስን ያመለክታል። ብዙውን ጊዜ፣ “ልጁ” ተብሎም ይጠራል

  • የእግዚአብሔር ልጅ የእግዚአብሔር ባሕርያት አሉት፤ እርሱ ፍጹም እግዚአብሔር ነው
  • እግዚአብሔር አብ፣ እግዚአብሔር ወልድና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሦስቱም በባሕርይ አንድ ናቸው
  • ከሰው ልጆች በተለየ መልኩ የእግዚአብሔር ልጅ ለዘላለም ነበር
  • በመጀመሪያ የእግዚአብሔር ልጅ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ዓለምን ፈጥሯል
  • ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ በመሆኑ፣ አባቱን ይወዳል፤ ለአባቱም ይታዘዛል፤ አባቱም ይወደዋል