am_tw/bible/kt/savior.md

822 B

አዳኝ

“አዳኝ” የሚለው ቃል ሌሎችን የሚያድን ወይም የሚታደግ ሰውን ያመለክታል። ለሌሎች ብርታትን ወይም የሚያስፈልጋቸውን የሚሰጥ ሰውንም ያመለክታል

  • ብዙ ጊዜ ከጠላቶቻቸው ስላዳናቸው፣ ብርታትንና ለመኖር የሚያስፈልጋቸውን ስለሰጣቸው ብሉይ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር የእስራኤል አዳኝ ተብሏል
  • አዲስ ኪዳን ውስጥ፣ “አዳኝ” የኢየሱስ ክርስቶስ መጠሪያ ነው፤ ምክንያቱም በኅጢአታቸው ምክንያት ለዘላላም ከመቀጣት ሰዎችን የሚያድን እርሱ በመሆኑ ነው። ከኅጢአታቸው ቁጥጥር ስር ከመሆንም ያድናቸዋል