# አዳኝ “አዳኝ” የሚለው ቃል ሌሎችን የሚያድን ወይም የሚታደግ ሰውን ያመለክታል። ለሌሎች ብርታትን ወይም የሚያስፈልጋቸውን የሚሰጥ ሰውንም ያመለክታል * ብዙ ጊዜ ከጠላቶቻቸው ስላዳናቸው፣ ብርታትንና ለመኖር የሚያስፈልጋቸውን ስለሰጣቸው ብሉይ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር የእስራኤል አዳኝ ተብሏል * አዲስ ኪዳን ውስጥ፣ “አዳኝ” የኢየሱስ ክርስቶስ መጠሪያ ነው፤ ምክንያቱም በኅጢአታቸው ምክንያት ለዘላላም ከመቀጣት ሰዎችን የሚያድን እርሱ በመሆኑ ነው። ከኅጢአታቸው ቁጥጥር ስር ከመሆንም ያድናቸዋል