am_tw/bible/kt/righthand.md

1.2 KiB

ቀኝ እጅ

“ቀኝ እጅ” የሚለው ምሳሌያዊ አነጋገር፣ በአንድ መሪ፣ ወይም ሥልጣን ባለው ሰው ቀኝ ያለውን የክብር ቦታ ያመለክታል።

  • ቀኝ እጅ” የሚለው ምሳሌያዊ አነጋገር፣ በአንድ መሪ፣ ወይም ሥልጣን ባለው ሰው ቀኝ ያለውን የክብር ቦታ ያመለክታል።
  • ቀኝ እጅ የኀይል፣ የሥልጣንና የብርታት ምሳሌ በመሆም ጥቅም ላይ ይውላል።
  • የአማኞች አካል ራስ እንደ መሆኑና ፍጥረትን ሁሉ የሚቆጣጠር እርሱ እንደ መሆኑ መጠን ኢየሱስ በእግዚአብሔር “ቀኝ እጅ” በኩል መቀመጡን መጽሐፍ ቅዱስ ያመለክታል።
  • በረከት በሚቀበል ሰው ራስ ላይ ቀኝ እጅ ማድረግ ያ ሰው ያለውን ልዩ የክብር ቦታ ያመለክታል (ለምሳሌ እስራኤል የዮሴፍ ልጅ ኤፍሬምን ስባርክ እንደ ታየው)።
  • በአንድ ሰው “ቀኝ እጅ በኩል ማገልገል” አገልግሎቱ ለዚያ ሰው በጣም ጠቃሚና ተፈላጊ መሆኑን ያመለክታል።