am_tw/bible/kt/remnant.md

1008 B

ትሩፍ፣ ትሩፋን

ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “ትሩፋን” ማለት፣ በጣም ብዙ ከሆነው ክፍል ወይም ወገን “የተረፉ” ወይም፣ “የቀሩ” ሰዎች ወይም ነገሮች ማለት ነው።

  • ብዙውን ጊዜ፣ “ትሩፋን” የሚያምለክተው ከአደገኛ ጥፋት የተረፉ ወይም በከፍተኛ ስደት ውስጥ እንኳ ለእግዚአብሔር ታማኝ የሆኑ ሰዎችን ነው።
  • ከውጪ ወራሪዎች ጥቃት ቢደርስባቸውም በሕይወት ኖረው ወደ ተስፋው ምድር የተመለሱትን አይሁድ ኢሳይያስ ትርፋን ይላቸዋል።
  • ጳውሎስ ጸጋውን ለመቀበል እግዚአብሔር የመረጣቸውን ሰዎች፣ “ትሩፋን” ይላቸዋል።
  • “ትሩፋን” የሚለው ታማኝ ያልሆኑ ወይም በሕይወት ያልተረፉ ወይም ያልተመረጡ ሌሎች መኖራቸውን ያመለክታል።