1008 B
1008 B
ትሩፍ፣ ትሩፋን
ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “ትሩፋን” ማለት፣ በጣም ብዙ ከሆነው ክፍል ወይም ወገን “የተረፉ” ወይም፣ “የቀሩ” ሰዎች ወይም ነገሮች ማለት ነው።
- ብዙውን ጊዜ፣ “ትሩፋን” የሚያምለክተው ከአደገኛ ጥፋት የተረፉ ወይም በከፍተኛ ስደት ውስጥ እንኳ ለእግዚአብሔር ታማኝ የሆኑ ሰዎችን ነው።
- ከውጪ ወራሪዎች ጥቃት ቢደርስባቸውም በሕይወት ኖረው ወደ ተስፋው ምድር የተመለሱትን አይሁድ ኢሳይያስ ትርፋን ይላቸዋል።
- ጳውሎስ ጸጋውን ለመቀበል እግዚአብሔር የመረጣቸውን ሰዎች፣ “ትሩፋን” ይላቸዋል።
- “ትሩፋን” የሚለው ታማኝ ያልሆኑ ወይም በሕይወት ያልተረፉ ወይም ያልተመረጡ ሌሎች መኖራቸውን ያመለክታል።