am_tw/bible/kt/purify.md

9 lines
1.4 KiB
Markdown

# ንጹሕ፣ ማንጻት
“ንጹሕ” መሆን እንከን የሌለው ወይም እዚይ ኣመገኘት ያልነበረበት የተቀላቀለ ነገር የሌለው ማለት ነው። አንድን ነገር ማንጻት ማለት ንጹሕ ማድረግና የሚያቆሽሸውንና የሚበክለውን ማንኛውንም ነገር ማስወገድ ማለት ነው።
* ከብሉይ ኪዳን ሕጎች አንጻር፣ “ማንጻት” በዋናነት ሕመምን፣ ከሰውነት የሚወጣ ፈሳሽን ወይም ልጅ መውለድን ከመሳሰሉ በሥርዓቱ ያረክሳሉ ከሚባሉ ነገሮች አንድ ነገር ወይም ሰው እንዲጠራ ማድረግ ማለት ነው።
* ብሉይ ኪዳን ሰዎች እንዴት ከኀጢአት መንጻት እንደሚችሉ ይናገራል፤ ብዙውን ጊዜ ይህ የሚሆነው እንስሳን መሥውሳዕት በማድረግ ነበር። ይህም ለጊዜው ብቻ የሚያገለግል በመሆኑ መሥዋዕቱ በየጊዜው መደጋገም ነበረበት።
* በአዲስ ኪዳን መሠረት መንጻት፣ የሚያመክተው ከኀጢአት መንጻትን ነው።
* ሰዎች ሙሉ ብሙሉና ለዘለቄታው ከኀቲአት መንጻት የሚችሉት በኢየሱስና በእርሱ መሥዋዕትነት በመታመን ንስሐ በማድረግና የእግዚአብሔርን ይቅርታ በመቀበል ብቻ ነው።