1.4 KiB
1.4 KiB
ንጹሕ፣ ማንጻት
“ንጹሕ” መሆን እንከን የሌለው ወይም እዚይ ኣመገኘት ያልነበረበት የተቀላቀለ ነገር የሌለው ማለት ነው። አንድን ነገር ማንጻት ማለት ንጹሕ ማድረግና የሚያቆሽሸውንና የሚበክለውን ማንኛውንም ነገር ማስወገድ ማለት ነው።
- ከብሉይ ኪዳን ሕጎች አንጻር፣ “ማንጻት” በዋናነት ሕመምን፣ ከሰውነት የሚወጣ ፈሳሽን ወይም ልጅ መውለድን ከመሳሰሉ በሥርዓቱ ያረክሳሉ ከሚባሉ ነገሮች አንድ ነገር ወይም ሰው እንዲጠራ ማድረግ ማለት ነው።
- ብሉይ ኪዳን ሰዎች እንዴት ከኀጢአት መንጻት እንደሚችሉ ይናገራል፤ ብዙውን ጊዜ ይህ የሚሆነው እንስሳን መሥውሳዕት በማድረግ ነበር። ይህም ለጊዜው ብቻ የሚያገለግል በመሆኑ መሥዋዕቱ በየጊዜው መደጋገም ነበረበት።
- በአዲስ ኪዳን መሠረት መንጻት፣ የሚያመክተው ከኀጢአት መንጻትን ነው።
- ሰዎች ሙሉ ብሙሉና ለዘለቄታው ከኀቲአት መንጻት የሚችሉት በኢየሱስና በእርሱ መሥዋዕትነት በመታመን ንስሐ በማድረግና የእግዚአብሔርን ይቅርታ በመቀበል ብቻ ነው።