am_tw/bible/kt/promise.md

612 B

ተስፋ ቃል

ተስፋ ቃል አንድን ነገር ለመስጠት ወይም ለማድረግ ቃል መግባት ማለት ነው። አንድ ሰው አንድ ነገር ለማድረግ ተስፋ ከሰጠ ያንን ለመፈጸም ይተጋል ማለት ነው።

  • መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ስለ ገባው ብዙ ተስፋ ቃል አስፍሮአል።
  • ተስፋ ቃል ኪዳንን በመሳሰሉ ውል ያላቸው ስምምነቶች ሁነኛ ክፍል ነው።
  • ብዙ ጊዜ የተስፋ ቃል እውን እንደሚሆን መሐላም ይኖረዋል።