am_tw/bible/kt/pharisee.md

9 lines
1.1 KiB
Markdown

# ፈሪሳዊ
ፈሪሳውያን ኢየሱስ በዚህ ምድር በነበረ ዘመን በጣም ታዋቂ የእስራኤል ሃይማኖት መሪዎች ነበር። አብዛኞቹ መካከለኛ ኑሮ ያላቸው ሠራተኞች ሲሆኑ፣ ጥቂቶቹም ካህናት ነበሩ።
* ከአይሁድ መሪዎች ሁሉ ፈሪሳውያን፣ ለሙሴ ሕግና ለሌሎቹ የአይሁድ ሕጎችና ወጎች በመታዘዝ ረገድ ፈሪሳውያን በጣም ጠንካሮች ነበር።
* የአይሁድ ሕዝብ በዙሪያው ከነበሩ አሕዛብ የተለየ ሆኖ እንዲዘልቅ በጣም ያስቡ ነበር። “ፈሪሳዊ” የሚለው ስም ራሱ፣ “መለየት” ከሚለው ቃል የመጣ ነበር።
* ፈሪሳውያን ከሞት በኋላ ሕይወት መኖሩን ያምኑ ነበር፤ መላእክትና ሌሎች መንፈሳዊ ፍጥረቶች መኖራቸውንም ያምኑ ነበር።
* የካህናት አለቆችን ጨምቶ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ኢየሱስንና የጥንት ክርስቲያኖችን አጥብቀው ይቃወሙ ነበር።