# ፈሪሳዊ ፈሪሳውያን ኢየሱስ በዚህ ምድር በነበረ ዘመን በጣም ታዋቂ የእስራኤል ሃይማኖት መሪዎች ነበር። አብዛኞቹ መካከለኛ ኑሮ ያላቸው ሠራተኞች ሲሆኑ፣ ጥቂቶቹም ካህናት ነበሩ። * ከአይሁድ መሪዎች ሁሉ ፈሪሳውያን፣ ለሙሴ ሕግና ለሌሎቹ የአይሁድ ሕጎችና ወጎች በመታዘዝ ረገድ ፈሪሳውያን በጣም ጠንካሮች ነበር። * የአይሁድ ሕዝብ በዙሪያው ከነበሩ አሕዛብ የተለየ ሆኖ እንዲዘልቅ በጣም ያስቡ ነበር። “ፈሪሳዊ” የሚለው ስም ራሱ፣ “መለየት” ከሚለው ቃል የመጣ ነበር። * ፈሪሳውያን ከሞት በኋላ ሕይወት መኖሩን ያምኑ ነበር፤ መላእክትና ሌሎች መንፈሳዊ ፍጥረቶች መኖራቸውንም ያምኑ ነበር። * የካህናት አለቆችን ጨምቶ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ኢየሱስንና የጥንት ክርስቲያኖችን አጥብቀው ይቃወሙ ነበር።