am_tw/bible/kt/peopleofgod.md

9 lines
1.2 KiB
Markdown

# የእግዚአብሔር ሕዝብ፣ ሕዝቤ
“የእግዚአብሔር ሕዝብ” የተሰኘው ሐረግ ከእርሱ ጋር የተለየ ግንኙነት እንዲኖረው እግዚአብሔር ከዓለም የጠራውን ሕዝብ ነው።
* እግዚአብሔር፣ “ሕዝቤ” ሲል እርሱ ስለ መረጠውና ከእርሱ ጋር ግንኙነት ስላለው ሕዝብ መናገሩ ነው።
* የእግዚአብሔር ሕዝብ በእርሱ ተመርጠዋል፤ እርሱን ደስ በሚያሰኝ መንገድ እንዲኖሩ ከዓለም ተለይተዋል። ልጆቼ በማለትም ይጠራቸዋል።
* በብሉይ ኪዳን፣ “የእግዚአብሔር ሕዝብ” የሚያመለክተው በእግዚአብሔር የተመረጡትንና እርሱን ለማገልገልና ለእርሱ ለመታዘዝ ከዓለም ሕዝብ መካከል ተለይተው የወቱትን የእስራኤል ሕዝብ ነው።
* በአዲስ ኪዳን፣ “የእግዚአብሔር ሕዝብ” በተለየ ሁኔታ የሚያመለክተው በኢየሱ የሚያምኑትን ሁሉ ሲሆን፣ ቤተ ክርስቲያን ተብለውም ይጠራሉ። ይህም አይሁድንና አሕዛብንም ይጨምራል።