am_tw/bible/kt/peopleofgod.md

1.2 KiB

የእግዚአብሔር ሕዝብ፣ ሕዝቤ

“የእግዚአብሔር ሕዝብ” የተሰኘው ሐረግ ከእርሱ ጋር የተለየ ግንኙነት እንዲኖረው እግዚአብሔር ከዓለም የጠራውን ሕዝብ ነው።

  • እግዚአብሔር፣ “ሕዝቤ” ሲል እርሱ ስለ መረጠውና ከእርሱ ጋር ግንኙነት ስላለው ሕዝብ መናገሩ ነው።
  • የእግዚአብሔር ሕዝብ በእርሱ ተመርጠዋል፤ እርሱን ደስ በሚያሰኝ መንገድ እንዲኖሩ ከዓለም ተለይተዋል። ልጆቼ በማለትም ይጠራቸዋል።
  • በብሉይ ኪዳን፣ “የእግዚአብሔር ሕዝብ” የሚያመለክተው በእግዚአብሔር የተመረጡትንና እርሱን ለማገልገልና ለእርሱ ለመታዘዝ ከዓለም ሕዝብ መካከል ተለይተው የወቱትን የእስራኤል ሕዝብ ነው።
  • በአዲስ ኪዳን፣ “የእግዚአብሔር ሕዝብ” በተለየ ሁኔታ የሚያመለክተው በኢየሱ የሚያምኑትን ሁሉ ሲሆን፣ ቤተ ክርስቲያን ተብለውም ይጠራሉ። ይህም አይሁድንና አሕዛብንም ይጨምራል።