am_tw/bible/kt/pentecost.md

885 B

ጴንጠቆስጤ (በዓለ ሃምሳ)፣ የሳምንቶች በዓል

በዓለ ሃምሳ ከፋሲካ ሃምሳ ቀን በኋላ የሚከበረው የአይሁድ በዓል ግሪክኛ ስም ነው።

  • የጴንጠቆስጤ ቀን የሳምንቶች በዓል የመጀመሪያው ቀን ነበር።
  • የሳምንቶች በዓል የሚከበረው የመከር ጊዜ ማብቂያን ለማሰብ ነው። በሙሴ በኩል እግዚአብሔር ሕጉን ለእስራኤላውያን በመጀመሪያ መስጠቱ የሚታሰብበት ጊዜ ነው።
  • ኢየሱስ ከሞት ከተነሣና ወደ ሰማይ ከተመለሰ በኋላ እግዚአብሔር በኢየሱስ ተከታዮች ላይ መንፈስ ቅዱስን ያፈሰሰው በዚህ ቀን በመሆኑ የጰንጠቆስጤ ቀን በአዲስ ኪዳን የተለየ ግምት ይሰጠዋል።