am_tw/bible/kt/pentecost.md

8 lines
885 B
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ጴንጠቆስጤ (በዓለ ሃምሳ)፣ የሳምንቶች በዓል
በዓለ ሃምሳ ከፋሲካ ሃምሳ ቀን በኋላ የሚከበረው የአይሁድ በዓል ግሪክኛ ስም ነው።
* የጴንጠቆስጤ ቀን የሳምንቶች በዓል የመጀመሪያው ቀን ነበር።
* የሳምንቶች በዓል የሚከበረው የመከር ጊዜ ማብቂያን ለማሰብ ነው። በሙሴ በኩል እግዚአብሔር ሕጉን ለእስራኤላውያን በመጀመሪያ መስጠቱ የሚታሰብበት ጊዜ ነው።
* ኢየሱስ ከሞት ከተነሣና ወደ ሰማይ ከተመለሰ በኋላ እግዚአብሔር በኢየሱስ ተከታዮች ላይ መንፈስ ቅዱስን ያፈሰሰው በዚህ ቀን በመሆኑ የጰንጠቆስጤ ቀን በአዲስ ኪዳን የተለየ ግምት ይሰጠዋል።