am_tw/bible/kt/nazirite.md

10 lines
1.2 KiB
Markdown

# ናዝራዊ፣ የናዝራዊ ስእለት
ናዝራዊ የሚባለው ናዝርውያን የሚሳሉትን ስእለት የተሳለ ሰው ነው።
* የናዝራዊ እስለት ከማንኛውም ከወይን የተሠራ መጠጥም ሆነ ምግብ መታቀብን፣ በስምምነት እስከ ተወሰነ ቀን ድረስ ማለት ሳምንቶች ወይም ወሮች ሊሆኑ ይችላሉ ጠጕርን አለመስተካከልን ይጨምራል። ወደ ሞተ ሰው አካል እንዳይቀርብም ይከለከላል።
* የተወሰነው ጊዜ ሲያበቃና ስእለቱም ሲፈጸም ናዝራዊው ወደ ካህን ሄዶ ቁርባን ያቀርባል። ጠጕሩን መቆረጥና ማቃጠልን ያካትትም ይሆናል። ሌሎች ገደቦች ሁሉ ይነሣሉ።
* የናዝራዊ ስእለትን በተመለከተ ሳምሶን በጣም የታወቀ የብሉይ ኪዳን ሰው ነው።
* መጥምቁ ዮሐንስም በሕይወት ዘመኑ ሁሉ የናዝራዊ ስእለት የነበረበት ሰው ሳይሆን አይቀርም።
* ሐዋርያው ጳውሎስም አንድ ወቅት ላይ ይህን ስእለት ሳያደርግ አልቀረም።